ለኢትዮጵያ ጫናዎች መፍትሄ የተጠራ ዉይይት
ሰኞ፣ ሰኔ 7 2013ማስታወቂያ
በመላ ዩናይትድስቴትስ የሚገኙ የማኅበረሰብና የተለያዩ አደረጃጀት መሪዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚሰነዘሩ ያልተገቡ ያሏቸውን ጫናዎችን መቋቋም በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መከሩ።በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አመራሮቹ ትናንት ባደረጉት የበይነ መረብ ውይይት በኢትዮጵያ ላይ እየተሰነዘረ ያለውን ጫና ለመቋቋም የሃገሪቱን አቋም የሚደግፉ ወዳጆችን ማፍራት የወጣቱን ድርሻም ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች ለማለፍ ፣በተቀናጀ መልኩ መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ