ለኢትዮጵያ ጥቃት የኤርትራ ምላሽ
ዓርብ፣ መጋቢት 7 2004ማስታወቂያ
ሳያገኝ ነዉ ብሎ እንደማያምንም አስታዉቀዋል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሐገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ የጦርነትን አስከፊነት የማያዉቅ ወደጦርነት ያምራ እንጂ ኤርትራ ይበቃታል፤ ለትንኮሳዉ ምልሽ አትሰጥም ብለዋል። ኢትዮጵያ የጥቃት ርምጃ ኤርትራ ላይ መሰንዘሯን መግለጿ ሁለቱ አገሮች ዳግም ወደሌላ ጦርነት ሊገቡ ይሆን ወይ የሚለዉን ስጋት አስነስቷል። ፈረንሳይ ሁለቱም ሐገሮች ለዉይይት እንዲቀመጡ ስትጠይቅ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ አደብ እንዲገዙ ተማፅናለች። ጣሊያንም እንዲሁ ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸዉ የተካረረዉን ዉጥረት እንዲያረግቡ አሳስባለች። የአውሮፓው ኅብረት የውጭ ፖለቲካ ኀላፊ ወ/ሮ ካትሪን ኤሽተንም ተመሳሳይ መልእክት ነው በመግለጫቸው ላይ ያስተላለፉት። የአፍሪቃዉን ቀንድ ፖለቲካ የሚከታተሉ ተንታኞች በበኩላቸዉ ለኢትዮጵያ ጥቃት ኤርትራ ወታደራዊ አፀፋ ላትመልስ ትችላለች ባይ ናቸዉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ገበያው ንጉሤ
ተክሌ የኋላ