ለስደተኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጀርመን
ረቡዕ፣ ኅዳር 29 2008ማስታወቂያ
ከቅርብ ወራት ወዲህ ጀርመን ለገቡ በርካታ ስደተኞች ጀርመናውያን ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ናቸው ። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስደተኞችን ያስተምራሉ ፣ ሀኪሞችና ነርሶች የነፃ ህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ ። ከፊሉ ባዶ ቤቱን ለቆላቸዋል ፣ ጡረታ የወጡ አስተማሪዎችም እውቃታቸውን በፈቃደኝነት እያጋሩ ነው ። እነዚህ ሁሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚከናወኑት ያለ መንግሥት እገዛ ነው ። በቅርቡ ደግሞ የኮምፕዩተር ጠበበት ወጣት ሥራ አጥ ስደተኞችን በኮምፕዩተር አሠልጥነው በሥራ ዓለም እንዲሰማሩ በማገዝ ላይ ናቸው ። ከዋና ከተማዋ በርሊን የመጣው ይህ ሃሳብ በኮሎኝ ከተማም ተግባራዊ ሆኗል ። የዛሬው ከኤኮኖሚው ዓለም ትኩረት ነው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አዘጋጅቶታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ