ሁከት በፍራንክፉርት
ሐሙስ፣ መጋቢት 10 2007ማስታወቂያ
የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ መከፈት ነው። ባንኩ የኢምፔሪያሊስቶች መጠቀሚያ ነው በማለት የአውሮጳ የዕዳ ቀውስን የሚመለከተውን አሠራር ለመቃወም ቁጥራቸው ወደ 20,000 የሚጠጋ የተቃውሞ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተው ነበር። ለተቃውሞ የተጠራው የአደባባይ ሰልፍ ግን የተጠናቀቀው ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና ፖሊሶችን ለግብግብ ቡጢ እና ቆመጥ ካስጨበጠ፣ ድንጋይ ካወራወረ፣ በርካቶችን ካስቆሰለ በኋላ ነበር። በግጭቱ ከ200 በላይ ሰልፈኞች እንዲሁም 150 ፖሊሶች መቁሰላቸው ተነግሯል። እንደ ፖሊስ ዘገባ ከሆነ 26 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የፍራንክፉርቱ ወኪላችን ጎይቶም ቢሆን ትናንት ሔሊኮፕተር በሰልፈኞቹ አናት ሲያንዣብብ፣ የፖሊስ መኪና በእሳት ሲያያዝ ሰልፉ በተኪያሄደበት ቦታ ተገኝቶ ነበር።
ተክሌ የኋላ
ጎይቶም ቢሆን
ማንተጋፍቶት ስለሺ