ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በደቡብ አፍሪቃ
ረቡዕ፣ ጳጉሜን 2 2008ማስታወቂያ
አገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው ዜጎች በሙሉ ከዚህ ወር ጀምሮ የእድሜ ማራዘሚያ መድሐኒት እንዲጠቀሙ አሳስባለች። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ መከላከያ ፅ/ቤት መረጃ አማካኝነት 180 000 ሰዎች ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ 2015 ዓ.ም. በኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ምክንያት ለሞት ተዳርገዋል። የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ መንግስታቸው በሽታውን ለመከላከል ቆርጦ መነሳቱን ለአገራቸው ምክር ቤት ተናግረዋል። የደቡብ አፍሪቃ ምክትል ፕሬዝዳንት የጤና ጉዳዮች አማካሪ ግን ዜጎች የግብረ-ስጋ ግንኙነት ሲፈፅሙ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
መላኩ አየለ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ